| |||||
![]() | |||||
ብሔራዊ ቋንቋዎች | መስኮብኛ, ኡድሙርትኛ | ||||
ዋና ከተማ | ኢዠቭስክ | ||||
ፕሬዝዳንት | አሌክሳንድር አሌክሳንድሮቪች ቮልኮቭ | ||||
ሊቀ መንበር | ዩሪ ስተፓኖቪች ፒትከቪች | ||||
የመሬት ስፋት | 42,100 ካሬ ኪ.ሜ. | ||||
የህዝብ ብዛት (2002) | 1,570,316 | ||||
ሰዓት_ክልል | +4 |
ኡድሙርትኛ የኡድሙርቶች ቋንቋ ነው። ኡድሙርቶች የኡድሙርቲያ ኗሪዎች ሲሆኑ ቋንቋቸው በፊኖ-ኡግሪክ ቋንቋ ቤተሰብ ውስጥ የተከተተ ነው። ኡድሙርቲያ በሩሲአ ውስጥ የሚገኝ ክፍላገር ሆኖ ኡድሙትኛ ከመስኮብኛ ጋራ መደበኛ ቋንቋዎቹ ናቸው። የሚጻፍበት በቂርሎስ ፊደል ነው። ቅርብ ዘመዶቹ ኮሚ እና ኮሚ-ፐርምያክ ቋንቋዎች ናቸው።
ቱርክመንኛ የቱርክምኒስታን ብሔራዊ ቋንቋ ነው። በቱርክመኒስታን 3,430,000 ተናጋሪዎች ሲኖሩ ከቱርክመኒስታን ውጭ ደግሞ 3 ሚሊዮን የሚያሕሉ ተናጋሪዎች በተለይም በኢራን (2 ሚሊዮን) በአፍጋኒስታን (500,000) እና በቱርክ (1000) አሉ።
ቱርክመንኛ በቱርክ ቋንቋ ቤተሰብ ውስጥ ይከተታል። ይህም አንዳንዴ በትልቁ አልታይ ቋንቋ ቤተሰብ ውስጥ ይደመራል። ቀድሞ የተጻፈበት ወይም በቂርሎስ ወይም በ አረብ ፊደሎች ነበር፤ አሁን ግን የቱርክመኒስታን መሪ ሳፓርሙራት ኒያዞቭ በላቲን ፊደል እንዲጻፍ አዋጀ። በ1994 አ.ም. ደግሞ የሳምንት ቀኖችና የወር ስሞች ሁሉ እንደ አቶ ኒያዞቭ "ሩህናማ" የሚባል ይፋዊ መጽሐፍ ፍልስፍና በአዋጅ ተቀየሩ።
ሎዥባን በ 1987 እ ኤ አ የተፈጠረ ሰው ሠራሽ ቋንቋ ነው። ቋንቋው የተፈጠረ በLLG ("ትክክለኛ አሰሳሰብ ያለው ቋንቋ ስብሰባ") በሚባል የዋሺንግተን ዲሲ ተቋም ነው። LLG በ1955 እ ኤ አ መጀመርያ የፈጠረ ቋንቋ "ሎግላን" ተባለ። ሎዥባን ከሎግላን ተሻሽሎ የወጣ ቋንቋ ይባላል።
አላማቸው ስዋሰው በሰዎችና በኮምፕዩተር በቀላል የሚታወቅ የ"ትክክለኛ አስተሠብ ቋንቋ" ለመፍጠር ነበር። ሌሎች ሰው ሰራሽ ቋንቋዎች ለምሳሌ ኤስፔራንቶ የተፈጠሩ በተለይ ከአውሮጳ ቋንቋዎች ቃላት በመልቀም ነበር። ሎዥባን ግን "ባሕላዊ ገለልተኝነት" ለማሳየት እየሞከረ ነው። ነገር ግን ብዙ የተማሩት ሰዎች ገና ስለሌሉ እስካሁን ከድረገጽ በቀር ምንም የተደረጀ ሥነጽሁፍ የለውም።
ቃላቱ የተፈጠሩ ብዙ ተናጋሪዎች ያላቸው የሰው ልጅ ቋንቋዎች በመነጻጸር ነበር። ለያንዳንዱ ቃል ስንት ድምጾች አንድላይ ከነዚህ ቋንቋዎች ጋራ እንዳለው ተቆጠረ። ስለዚህ ቻይነኛ ከሁሉ ብዙ ተናጋሪዎች ስላለው ብዙ ድምጾች የተለቀሙ ከቻይነኛ ነበር። ስዋሰው እንደ ኮምፕዩተር ቋንቋ ይመስላል።
ምሳሌ ዐረፍተ ነገሮች
- "ብራማው" - ይበልጣል።
- "ሚ ብራማው ዶ ለ ካ ሽላኒ" - በቁመት ረገድ እኔ ካንተ እበልጣለሁ።
- "ለ ሺንፎ ሹ ብራማው ለ ምላቱ" - አንበሣው ከድመቱ ይበልጣል።
- "ሚ ብራማውጋው ለ ሺንፎ ለ ምላቱ" - አንበሣውን ከድመቱ እንዲበልጥ አደርጋለሁ።